በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የሚቀጥሉትን አምስት ዓ...

image description
image description
image description
image description
- Recent News   

በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የሚቀጥሉትን አምስት ዓመታት የልማት አቅጣጫ የሚያሳይ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

 

የዕቅድ ውይይቱን አቶ ምስክር ታዬ (የማዕከሉ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር) ያቀረቡ ሲሆን በውይይቱም የዕፅዋት ምርምር፣ የሆርቲካልቸር፣ የኢኮ-ቱሪዝም፣ እና የብዝሀ ህይወት ትምህርት እቅዶች ላይ በስፋት የተወያዩ ሲሆን ሀገር በቀል ዕፅዋትን ለማሰባሰብ ፣በስም ለመለየት፣ ደረቅ ናሙና ለመሰብሰብ ፣የአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራዎችን ከፍ ለማድረግ፣ የዕፅዋት ብዜት ለማከናወን በማዕከሉ ውስጥ የችግኝ ተከላ በማድረግ እንክብካቤ ማድረግ፣ በከተማ ግብርና አትክልት ልማትን ለማሳደግ ፣የተለያዩ የፍራፍሬ ዝርያዎቸን የማሰባሰብ ስራ ለማካሄድ፣ በማዕከሉ የደን ክልሎች ወራሪ ዕፅዋትን እና አረምን ደጋግሞ ማስወገድ፤ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች ጋር ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ማዘጋጀት፣ የጎብኚዎችን ደህንነት መጠበቅ፣ የተቋሙን አጠቃላይ ደህንነት መጠበቅ ፣የኢኮ ቱሪዝም ስራዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች ማስተዋወቅ፣ እንዲሁም የክትትትል እና ድጋፍ አግባብን በተመለከተ በአምስት ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ በማዕከሉ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት ሰፊ ውይት ተደረጎበታል፡፡

ተሳታፊዎችም በዕቅዱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶችን በማቅረብ፣ ዕቅዱ ተግባራዊና ውጤታማ እንዲሆን በትብብር መስራት ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል።

የአምስት ዓመቱ ዕቅድ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን የልማት አቅም በማሳደግ፣ የአረንጓዴ አካባቢ ልማትን በማጠናከር እና ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ግብ ስኬት የሚያበረክተውን ሚና ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።